water treatment
👉 Water Treatment ፨ የላእላይ ምድር ውሃን (surface water) ለማጣራት የምንጠቀማቸው ዘዴዎች ክቅደም ተከተል ፨ . ~ ስክሪኒንግ (screening) - ይህ የመጀመረርያው የማጣራት ደረጃ ሲሆን በዚህ የማጣራት ዘዴ ውስጥ በውሃው ላይ የሚንሳፈፉ ግዙፍ አካላትን ለምሳሌ የዛፍ ጉቶ ፣ግንድ፣ ቅጠል እና ልዩ ልዩ የፕላስቲክ ተንሳፋፊ ቁሳቁሶች ወደ ዋናው የማጣሪያ ገንዳ እና ስርዓት እንዳይገቡ ያግዳል ። . ~ ማርጋት (Coagulation )፦ በዚህ የማጣራት ደረጃ ላይ ለአይን እይታ ያነሱ ጥቃቅን አካላትን (Particle size 10^-7cm የሚሆኑ) በማርጋት እና የኬሚካል ቻርጃቸውን ኒውትራላይዝ የሚያረግ ኬሚካል በመጨመር እርስ በእርሳቸው እንዲሳሳቡ ማድረግ ነው ። ለዚህ የአልሙኒየም ፖሊመሮች (Alum) እና አይረን (Fe+3) አገልግሎት ላይ ይውላሉ። እንደ የቁልቋል ተክል ያሉ የተፈጥሮ አርጊዎች (coagulants) መጠቀምም ይቻላል ( በዚህ ፔጅ ቁልቋልን እንዴት ተጠቅመን ንፁ ውሃ ማግኘት እንደምንችል አይተናል ) . ~ ጉግለት (Flocculation)፦ ይህ እርከን ፤ ማርጋት(coagulation ) ወቅት የረጉ ጥቃቅን አካላትን እርስ በእርሳቸው ቦንድ እስኪፈጥሩ እና እርስ በእርሳቸው ተጣብቀው እስኪጓግሉ ውሃው በተለያየ ፍጥነት የሚማሰልበት ነው። ይህ ዘዴ ሜካኒካል ወይም ማኑዋል በሆነ መልኩ ይተገበራል ። . ~ መዝቀጥ/ማዝቀጥ (sedimentation) ፦ በፍሎኩሌሽን ወቅት የጓጎለው ጥቃቅን አካላት በዚህን የማጣራት ደረጃ እንዲዘቅጡ ይደረጋል ። ይህ ዘዴ የሚተገበረው የሚጣራው የውሃን ፍጥነት በመቀነስ ግራቪቲን ተጠቅሞ እንዲዘቅጥ ማድረግ ነው። በግራቪቲ ለማዝቀጥ የሚከብ...